በኢሴልድ/EWDO ሃገር አቀፍ የፓናል ውይይት ተካሄደ
የዘንድሮው ማርች 8 በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ "’ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’በሚል የተመረጠውን መሪ ቃል መሰረት በማድረግ ከኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ ጋ በመቀናጀት ሃገር አቀፍ ፓናል ውይይት አዘጋጅታለች፡፡
የፓናል ውይይት ርእስ ፡ -የሥርዓተ ፆታ እኩልነት እና የሴቶች መብትን በኢትዮጵያ ማሳደግ፡ ተግዳሮትና እና እድሎች በሚል የፓናል ማወያያ አርእስት የተለያዩ ፓናሊስቶች መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል በዚህም መሰረት ሰብአዊ መብቶች እና የስርዓተ ጾታ እኩልነት በኢትዮጵያ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን ክብርት የሴቶችና አካልጉዳተኞች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሃዋርያ ማህበራዊ ደንቦች እና የፆታ እኩልነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ሥነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው የልጆች አስተዳደግ እና የጾታ እኩልነትዶ/ር ታምራት ዘላለም በፌደራልና በአ/አበባ ከተማ አ/ር ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ላይ ሰርተዋል፡፡
ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎች እና የአፈፃፀም ተግዳሮቶች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አሸነፈች አበበ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ የሃይማት አባቶች የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የህብረተብ ክፍሎች ወኪሎች የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት መሪዎች አመራሮች ተማሪዎች ከሁሉም የሃገሪቱ የተጋበዙ የክልል አደረጃጀት መሪዎች ወዘተ የተገኙ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላፉት የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ሁሉአገርሽ ታዘዝ ሲሆኑ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአ/አባበ ከተማ ም/ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር ናቸው፡፡

Leave a Reply