የስነዜጋና የስነ ምግባር ስልጠና ንቁ የምርጫ ተሳትፎን ለማበረታታት
የኢትዮጵያ ሴቶች ልማት ድርጅት (EWDO)ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር መምህራን ማህበር ጋ በመቀናጀት ከNational Election Board of Ethiopia ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ እና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት በተሰጠው ፈቃድ መሠረት፣ ዛሬ ከቦሌ የካፐእና ለሚኩራ ክፍለ ከተሞች ስር ከሚገኙ ት/ቤቶች ለተውጣጡ መምህራንና የት/ቤት አስተዳደር አመራሮች በስነ-ዜጋ እና በመራጮች ትምህርት ማንዋል ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናው የዜጎችን የምርጫ ግንዛቤ ለማሳደግ፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ለማበረታታት እና ትክክለኛ የመራጮች ትምህርት ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ ያግዛል። ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ እንድንሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር መምህራን ማህበር ላደረጉልን ትብብብር እናመሠግናለን።